Fana: At a Speed of Life!

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ለ293 ሺህ ዜጎች የሥራ ዕድል ተፈጠረ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከ293 ሺህ በላይ ዜጎች የሥራ ዕድል እንደተፈጠረላቸው የክልሉ ሥራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ አስታውቋል።

የቢሮው ሃላፊ አቶ ሙስጠፋ ኢሳ እንዳሉት÷ በበጀት ዓመቱ ከ350 ሺህ በላይ ዜጎችን የሥራ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ ነው።

ባለፉት ዘጠኝ ወራትም 293 ሺህ 455 ዜጎችን ቋሚና ጊዜያዊ የሥራ ዕድል ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን ተናግረዋል።

ከእነዚህ ውስጥም 223 ሺህ ዜጎች በቋሚነት እንዲሁም 31 ሺህ የሚሆኑት ደግሞ የውጭ ሀገራት ሕጋዊ የሥራ ስምሪት ያገኙ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

ግብርና፣ ኢንዱስትሪ፣ የአገልግሎት ዘርፎች፣ የኮሪደር ልማት እና የሀገር ውስጥ እንዲሁም የውጭ ሕጋዊ የሥራ ስምሪት የሥራ ዕድል የተፈጠረባቸው መስኮች ናቸው ብለዋል።

የሥራ ዕድል ፈጠራ ጉዳይ በሴክተር ብቻ የሚታጠር አይደለም ያሉት ሃላፊው÷ በክልሉ የሚገኙ ባለድርሻዎችም የበኩላቸውን ሚና እየተወጡ መሆኑን አንስተዋል፡፡

ዘርፉን ለማጠናከር የተዘዋዋሪ ብድር ፈንድን የማስመለስና ለበርካታ ዓመታት የተያዙ ሼዶችን በማስለቀቅ ለአዳዲሶች የማሸጋገር ሥራ መሰራቱን ገልፀዋል።

ከ621 ሚሊየን ብር በላይ ብድር መሰራጨቱን ጠቅሰው÷ ከ550 በላይ የመስሪያና የመሸጫ ሼዶችን በማስመለስ ለአዲስ ሥራ ፈጣሪዎች የማቅረብ ሥራ መሰራቱንም ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.