Fana: At a Speed of Life!

የጎንደር ከተማ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የጎንደር ከተማ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር እየተካሄደ ይገኛል።

በመርሐ ግብሩ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች መገኘታቸውን በብልጽግና ፓርቲ አማራ ክልል ቅ/ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ እየተካሄደ የሚገኘው የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር በከተማዋ ገቢው ለሁለተኛው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት ሥራ ለማከናወን የሚውል እንደሆነ ተገልጿል።

ሁለተኛው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት ሥራ 12 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው ሲሆን፤ 1 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር በጀት እንደሚጠይቅ ከተማ አስተዳደሩ መግለጹ ይታወሳል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.