ለጎንደር ከተማ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር ከ2 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ተሰበሰበ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) “ኑ ጎንደርን እንሞሽር” በሚል መሪ ሐሳብ የተካሄደው የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር ከ2 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ በማሰባሰብ ተጠናቋል።
በዛሬው የገንዘብ ማሠባቢያ መርሐ ግብር ከ2 ሺህ ብር እስከ 1 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ድጋፍ መደረጉ ተገልጿል።
በመርሐ ግብሩ ከስድስት ዓመት ታዳጊ እስከ ሀገር ሽማግሌዎች መሳተፋቸውን እንዲሁም በሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጭ ያሉ ወገኖች መሳተፋቸውን አሚኮ ዘግቧል።
“ኑ ጎንደርን እንሞሽር” ታላቅ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር እስከ ግንቦት 30/2017 ዓ.ም ድረስ በተለያዩ መርሐ ግብሮች ይቀጥላልም ተብሏል።