ከ5 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ ባለሃብቶች ወደ ሥራ ገብተዋል
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 21፣2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት ከ5 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ 88 የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ወደ ሥራ መግባታቸውን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ንግድና ኢንቨስትመንት ቢሮ አስታወቀ፡፡
ፕሮጀክቶቹ የተሰማሩትም በግብርና፣ በኢንዱስትሪ እና በአገልግሎት ዘርፍ መሆኑን የቢሮው ምክትል ኃላፊ ከበደ ተስፋዬ ተናግረዋል፡፡
በኢንቨስትመንት ዘርፍ እንዲሰማሩ ፈቃድ ተሰጥቷቸው ውሳኔ ላገኙ ፕሮጀክቶችም 13 ሺህ 763 ሔክታር ተላልፏል ማለታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡
በሌላ በኩል በተወሰደው ሕጋዊ ርምጃ 20 የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ውላቸው መቋረጡን እና ፈቃድ ወስደው ፈጥነው ወደ ሥራ የሚሰማሩ ባለሀብቶችን እንደሚያበረታቱ ጠቁመዋል፡፡