በአማራ ክልል በተለያዩ ከተሞች ሕዝባዊ ውይይቶች ተካሄዱ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአማራ ክልል በተለያዩ ከተሞች ሕዝባዊ የውይይት መድረኮች ተካሂደዋል።
በውይይት መድረኮቹ ላይ “የጥፋት እጆች እና መዘዞቹ” የተሰኘ ዘጋቢ ፊልም ቀርቦ ከተሳታፊዎች ጋር በተደረገ ውይይት ተሳታፊዎቹ ለሰላም ዘብ ለመቆም ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።
ከዘጋቢ ፊልሙ የጥፋትን አስከፊነት እና የሰላምን አስፈላጊነት እንደተገነዘቡበት የውይይቱ ተሳታፊዎች ለአሚኮ በሰጡት አስተያየት ገልጸዋል፡፡
በርካታ ትምህርት ቤቶች እና በርካታ መሠረተ ልማቶች መቋረጣቸውን መመልከታቸውንም ጠቁመዋል፡፡
የሕዝብ ፍልሰትንም እንደተመለከቱ ጠቁመው፤ ማኅበረሰቡ ሰላምን እንደሚሻ እና ለዚህም ቁርጠኛ መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡
ከሰው ልጅ የማይጠበቅ ዘግናኝ ድርጊቶችን ተፈጽመው በማየታቸው ማዘናቸውን የገለጹት የውይይቶቹ ተሳታፊዎች፤ ጦርነት ለማንም አይበጅምና ሁሉም ሰላምን ለማስፈን መሥራት እንደሚጠበቅበት አስገንዝበዋል፡፡