Fana: At a Speed of Life!

መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የብልፅግና እሳቤዎች በተግባር የሚታዩበት ነው – አቶ አደም ፋራህ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የብልፅግና መሰረታዊ እሳቤዎች በተግባር የሚታዩበት መሆኑን በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ ገለፁ።

ብልፅግና ፓርቲን ጨምሮ የተለያዩ የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲ አመራር አባላት የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ማዕከልን ጎብኝተዋል።

አቶ አደም ፋራህ በዚሁ ወቅት፤ የአንድ ማዕከል አገልግሎቱ ሰው ተኮር መሆኑን ጠቅሰው፤ በዚህም ሁሉንም ዜጋ በእኩልነትና በፍትሃዊነት የሚያገለግል ሀገራዊ ተቋም ነው ብለዋል።

የመንግስትን አገልግሎቶች በቴክኖሎጂ የታገዙ ፈጣን፣ ቀልጣፋ እንዲሁም የጥራት ደረጃውን ያሟሉ እንዲሆኑ ሰራተኞችን ከማሰልጠን ባለፈ የተጠያቂነት አሰራር እንዲሰፍን መደረጉን ማብራራታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በማዕከሉ ኃላፊነትን በብቃት መወጣት የሚችሉ ባለሙያዎች መኖራቸው መንግስት ለተቋማት ግንባታ የሰጠውን ትኩረት ማሳያ ነው ብለዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.