Fana: At a Speed of Life!

የከተማ አስተዳደሩ ምክር ቤት ከ11 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር በላይ ተጨማሪ በጀት አጸደቀ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 22፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት 11 ቢሊየን 556 ሚሊየን 999 ሺህ ብር ተጨማሪ በጀት በሙሉ ድምፅ አፅድቋል።

ምክር ቤት በከተማዋ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎችን ለመደገፍ የቀረበለትን ተጨማሪ በጀት ያጸደቀ ሲሆን÷ በጀቱ ለመደበኛ እና ለካፒታል ወጭ ይውላል ተብሏል።

ከተማ አስተዳደሩ በበጀት ዓመቱ መጀመሪያ ከ230 ቢሊየን ብር በላይ በጀት አፅድቆ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱም ተነስቷል።

ምክር ቤቱ የተለያዩ ሹመቶችን በማጽደቅ የተጠናቀቀ ሲሆን፤ በዚሁ መሠረት ወ/ሮ ቆንጂት ደበላ ዎላ – የአዲስ አበባከተማ አስተዳደር የሴቶች፣ ሕጻናትና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ (በሽግሽግ) እንዲሁም አቶ አወሌህ መሐመድ ኦመር – የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል፡፡

በተጨማሪም ወ/ሮ አይሻ መሐመድ አደን – የአዲስ አበባከተማ አስተዳደር የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር፣ ሕይወት ሣሙኤል ጸጋዬ (ኢ/ር) – የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር እና ሲ/ር ሶፊያ አለሙ – የሴቶች፣ የወጣቶችና ህፃናት ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ሆነው መሾማቸው ተገልጿል፡፡

በሚኪያስ ዓለሙ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.