Fana: At a Speed of Life!

ዳሸን ባንክ 40 ሚሊየን ዶላር የንግድ ፋይናንስ ዋስትና ብድር አገኘ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 22፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአፍሪካ ልማት ባንክ ለዳሸን ባንክ 40 ሚሊየን ዶላር የንግድ ፋይናንስ ዋስትና ብድር ማጽደቁን አስታውቋል፡፡

የብድር ስምምነቱ በአኅጉራዊና በዓለም አቀፍ ደረጃ የንግድ አገልግሎቶችን ለማስፋፋት የጎላ ሚና እንዳለው የገለጹት የዳሽን ባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አስፋው ዓለሙ፤ በተጨማሪም የኢትዮጵያን የፋይናንስ ዘርፍ ለማጠናከር ያስችላል ብለዋል፡፡

የአፍሪካ ልማት ባንክ ፋይናንስ ሴክተር የልማት ዳይልክተር አሕመድ አቶት በበኩላቸው፤  ብድሩ አነስተኛ ፣ መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችን እና የሀገር ውስጥ ኮርፖሬሽኖችን ለመደገፍ ያለመ ትልቅ እርምጃ መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡

ዳሸን ባንክ ያገኘው ድጋፍ የገቢና ወጪ ንግድ ፋይናንስ መስፈርቶችን እንዲሳለጥ በማድረግ የኢትዮጵያ ወሳኝ የኢኮኖሚ ዘርፎች ለመደገፍ እንደሚያስችልም ተናግረዋል፡፡

የአፍሪካ ልማት ባንክ የፈቀደው የንግድ ፋይናንስ ዋስትና ብድር፤ እንደ ማዳበሪያ፣ ፋርማሲዩቲካል፣ የፀሐይ ኃይል ፖኔሎችንና ማሽነሪዎችን ወደ ሀገር ቤት ለማስገባት ድጋፍ ያደርጋል ተብሏል፡፡

በእዮናዳብ አንዱዓለም

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.