ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የመጀመሪያዎቹን 12 የሱ-35 4ኛ++ ትውልድ የጦር ጄቶች ርክክብን በተመለከተ ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች፡- On Oct 28, 2026 68 ከጥቂት ዓመታት በፊት አጠቃላይ የኢትዮጵያን ስጋት ለመቀነስ እንዲሁም በዓለም ሀገራት ዘንድ የአየር የበላይነትን ለመውስደ የሚደረገውን ሩጫ በመገንዘብ ከሩሲያ መንግሥት ጋር የሱ-35 4ኛ ትውልድ ኤር ክራፍት ስምምነት ፈጽመን ነበር፡፡ ስምምነቱ ጊዜው ደርሶ የመጀሪያው ዴሊቨሪ ስምምነት በ2027 ቢሆንም ከሬዚዳንት ፑቲን ጋር በህንድ በነበረን ቆይታ ቅድሚያ ሰጥተው እንዲያቀርቡልን ባቀረብነው መሰረት የመጀመሪያውን ሱ-35 ተረክበናል፡፡ በመጀመሪያው ዙር 12 የሱ ሶስት ኤርክራፍቶችን እንዲሁም አራት ኤስ 400 የአየር መከላከያ ስርዓቶችን ትረከባለች፣ እነዚህ አቅሞች ለኢትዮጵያ ትልቅ ትርጉም አላቸው፡፡ በተለያዩ ሀገራት በግጭት ጊዜ ያለው ምስቅልቅል ችግር ከመፈጠሩ በፊት በሰላሙ ጊዜ መደረግ የሚገባውን ዝግጅት ካለማድረግ የሚመጣ ነው፡፡ ኢትዮጵያ በብዙ ጠላት የተከበበች ሀገር ናት፣ ልጆቻችን ሀገር እንዲኖራቸው፣ የአየር ክልላችን እንዳይደፈር በቂ ዝግጅት ማድረግ ይጠበቅብናል፡፡ ይህ የምናየው የሱ 35 ኤር ክራፍት በዓለም ላይ ምርጡ የሚባለው የዘመኑን ቴክኖሎጂ የታጠቀ ኤር ክራፍት ነው፤ የአየር እና የምድር ውጊያዎችን ማድረግ ይችላል፡፡ እንዲሁም የክሩዝ ሚሳኤሎችን የማክሼፍ አቅም ያለው ጄት ነው፤ ክሩዝ ሚሳኤሎችን እስከ 200 ኪሎ ሜትር ድረስ መነሻቸውን በማጥናት ማምከን የሚችል ነው፡፡ ይህን የአየር መከላከል አቅም ካልገነባን እንደ ሀገር ህልውናችንን ለማስቀጠል እንቸገራለን፤ በዚህ ምክንያት ሰው ስናሰለጥን ቆይተናል፤ አሁን የታጠቅናቸው ሱ-35ቶች በበቂ ሁኔታ የኢትዮጵያን የአየር ክልሎች ለመከላከል ያግዛሉ፡፡ በቂ የጦር አቅም ያላቸው ሀገራት በቀላሉ አይደፈሩም፤ ያልተዘጋጀ መንግሥት ውጊያን ይጋብዛል፤ የተዘጋጀ ግን ውጊያን ያስቀራል፤ ከዚህ አንፃር የዛሬው ስምምነት ከፍተኛ ትርጉም አለው፡፡ በሰብ ሰሃራ አፍሪካ ኢትዮጵያ የሱ- 35 የታጠቀች ብቸኛዋ ሀገር ናት፤ በድሮን ብቻ ሳይሆን በሱ 34 እና 35 የአየር የበላይነቷን እያረጋገጠች ትገኛለች፡፡ #ኢትዮጵያ #ትልቅሀገር #ትልቅሕዝብ #ታላቅርዕይ በሚኪያስ አየለ 68 Share FacebookTwitterTelegramWhatsAppEmailViberPrint