Fana: At a Speed of Life!

ስደተኞችን እና ከስደት ተመላሾችን የስራ እድል ተጠቃሚ የሚያደርግ የትብብር ስምምነት ተፈረመ

አዲ አበባ፣ መስከረም 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የተጠለሉ ዓለም አቀፍ ስደተኞችን እንዲሁም ከስደት የተመለሱ ኢትዮጵያውያንን በስራ እድል ፈጠራ ተጠቃሚ የሚያደርግ የትብብር ስምምነት በስራ እድል ፈጠራ ኮሚሽን እና በስደተኞች እና ከስደት ተመላሾች ጉዳይ ኤጀንሲ መካከል ስምምነት ተፈረመ፡፡
ተቋማቱ የተሰጣቸውን ተልዕኮ በቅንጅት ለማከናወን ስምምነቱ ይረዳቸዋል ተብሏል።
ከዚህም ባለፈ የስራ ገበያው ያለበትን የአካታችነት ችግር ለመቅረፍ እንደሚያግዝም ተገልጿል።
ስደተኞች እና ከስደት ተመላሾች ከማህበረሰቡ ጋር ያላቸውን ኢኮኖሚያዊ መስተጋብር የሚያሻሽል ስምምነት ነውም ተብሏል።
በስራ ገበያው ውስጥ እምቅ ሃብትን በመለየት በግብርና፣ ኢንዱስትሪ እና አገልግሎት ዘርፍ የስራ ገበያዎች ላይ በማተኮር እንደሚሰራ የስራ እድል ፈጠራ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ንጉሱ ጥላሁን ገልጸዋል።
የስደተኞች እና ከስደት ተመላሾች ጉዳይ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ጎበዛይ በበኩላቸው÷ በአሁኑ ወቅት በአጠቃላይ ከ900 ሺህ በላይ ስደተኞች ኢትዮጵያ ውስጥ መኖራቸውን እና ባለፉት 4 ዓመታት ብቻ ወደ ግማሽ ሚሊየን የሚጠጉ ዜጎችም ወደ ሃገር መመለሳቸውን አንስተዋል።
ዛሬ ከስራ እድል ፈጠራ ኮሚሽን ጋር የተፈጸመው ስምምነትም የእነዚህን ዜጎች የስራ እና የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት የተሻለ የሚያደርግ ነው ብለዋል።
ስምምነቱ የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግብ ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እና ከለጋሾች ብዙ ይጠበቃል ሲሉም አቶ ተስፋዬ አሳስበዋል ሲል ኢቢሲ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.